ለምን ይፍረስ ?
                   (አጭር ታሪክ) ምናባዊ           በ ናሙስ ናን

ተሸፋፍኘ አንደተኛሁ ነበር ከውጭ የሚጠራኝ ሰው አንዳለ የተረዳሁት።አህተ ነበረች።ያው “ቁርስ ደርሷል” ልትለኝ ነው።የአየሩ መቀዝቀዝ ተከትሎ አጆቼ ጉልበቴን የሙጥኝ አቅፈው—አይኖቼ ብርድልብስ  ዉስጥ ሌባና ፖሊስ ይጫወቱ ይመስል—ተጨናንቆ  ባደረው አአምሮዬ የተቦኩ የሃሳብ ድሪቶች አያሰሱ ይሆናል።ከ 6 ዓመት በሁውላ ነው ቤተሰቦቼን የተገናኘሁት።ከትላንት በስትያ  አንደመጣሁ ሰፈሩ ብዙ ተቀይሮ አላገኘሁትም።አንደመጣሁ ተከርችሞ የሰነበተው የ አቢ ተማም ያረጀች ጎጆ ላይ ነበር ቀልቤ ያረፈው።የአርሳቸው ቤት ከኛ ቤት ቀጥሎ ነው ያለው።

———————————————————————————————-  ———  —– —————–
የተኛሁበት ክፍል በጣም ጠባብ ነች።ያኔ ከሰፈር ከመራቄ  በፊት አዚህ ነበር የማርፈው።አዳር የለበስኩት አንሶላ ገፈፍ አድርጌ አይኔ ግድግዳው ላይ አረፈ። 3 በሸራ የተሰሩ ስአሎች ፈገግታ ርቋቸው — የፀሐይ ብርሃን ተርበው —አጅግ ወይበው ይታዩኛል።የ አቢ ተማም አጅ የ ስነ ፅሁፍ ዓይን የሚኳልበት ድንቅ አጅ ነበር።ዉስጤ ጭንቀት ሞላኝ።አአምሮዬ ሰላም አጣ።አይኖቼ አንባ አረገዙ።ቁጭት—ቁጭት—“ባይሆንስ” የሚል  ፍጭት ከራሴ ገጠምኩ።አውቄ ቁርስ ላለመብላት አረፋፈድኩ።ሆኖም መተኛቱ አልወደድኩትም።አዚህ ተኝቼ ምንም አልሰራም።ስለዚህ ወደ ዉጭ መውጣት አለብኝ።ወጥቼ የቅያስ መንገዱን ተከትዬ ዋናውን አስፋልት አንደወጣሁ ዉስጠቴ ወደ አገና -ማዞርያ መታጠፍ አንዳለብኝ ይነግረኛል።መሄድ ጀመርኩ።—-ደረስኩ።አስፋልቱ በሰው ትርምስ ሰላሙን አንዳጣ ያስታውቅበታል። ከሰማይ አሞሮች ያንዣብባሉ። አይነ መሬት ላይ ከቀረው የአሞሮቹ ምስል አያንከራተትኩ —‘አሞራ ብሆንስ?’ የሚል የዉስጥ ሃሳቤ ለአቅመ-ንግግር ሳይደርስ ቀርቶ ዋጥኩት።ብሆን ግን ከላይ ወደታች ሳይ አስፋልቱ አንድ አጁ ያጣ ‘ተ’ ፊደል ቅርፅ ሳይኖረው አይቀርም ብዬ አስብኩ።

                                “ሰሚር”——–ከሃሳቤ መንጭቆ ያወጣኝ ጥሪ።አበራ ከበስተኋላዬ አየተከተለኝ ኖሯል።ባልሰማ አይነት ዝም አላልኩትም።ተገናኝን።አየተንሰፈሰፈ አናገረኝ።የድሮ ወዳጄ ።ብዙ አንደተቻወትን———
                         ” አረስቼው –ከቤት ጥራው ተብዬ ነው የተከተልኩህ—ግን አንተ አንዴት ነህ?”
ጥሩ ስሜት ላይ ስላልነበርኩ ልሂድ አልሂድ አያልኩ ጥቂት ተወዛገብኩ።
                             “ለምን ፈለጉኝ?”   አልኩት።
                             
                             “የ አቢ ተማም ቤት ሊፈርስ መሰለኝ —-”  አንገቱን ደፍቶ።
                             “ለምን?” ጮህኩበት አሱ ያፈረሰው መሰለብኝ።
                             “አኔ’ጃ “
‘ድንቄም  ማፍረስ’ —-በሃሳቤ– በፍጥነት ቤት ሄድኩ።
ብዙ ሰው ተሰብስቧል።ያወራሉ።ይተነብያሉ።ብዙ ብዙ—–

                                         “ማን ተጠግቶ ነው የሚነካው?”
                                         “ስንት ዓመት የተዘጋ ቤት—የ አጋንንት መናሀርያ።”
                                          “ቢቀርስ —-የጠንቅዋይ ቤት ከመነካካት ኤድያ —“
                                          
                                         “ልጁ መጣ መሰለኝ አሱ አንደሆነ ከሽማግለው በምን ተሽሎ–“
የሚያወሩት ይዘገንናል። አያዳምጡም ።
———————     ————-    —————–   ————- ———–   ————–     ————-

የኔ መምጣት የፈለጉት ለሌላ አይደለም።ቤቱን ከፍቼ።ውስጥ ያለውን አይተው ለማፍረስ—። ‘አቢ ተማም’ አባቴ ይሁኑ አያቴ —-ዘመድ ይሁኑ ባዳ የማውቀው ነገር የለም። በሕይወት አያሉ ከሳቸው አሳልፍ ነበር። በዚህ የተነሳ ከአባቴ ብዙ ችግር ውስጥ ገብቻለሁ።ታታሪ ነበሩ።ጥበብ አፍቃሪ።ሩህሩህ–ቸርና ለጋስ አረጋዊ።ይህን ሁል ግን በሕይወት በነበሩ ሰዓት ያወቀው አልነበረም።ፈረንጅ መጥቶ ስለርሳቸው ስላልፃፈ ይሆናል—ወይም –? ሁሌም በመጥፎ ስም ሲጠሩ ኖሩ ጥበብን ባወቁ።ተሰደቡ።

—————————-      ————————-     ———————-    —————- ———————-
አንድ ቀን ብዙ አጫወቱኝ።ስለ ጠልሰም አውቀት አንኩአን ሰምቸው በምናብ የማላስበውን ቁምነገር አወጉኝ።

“ይህ ጥበብ በ ዘር የሚተላለፍ አንጂ አንዲሁ የሚለቀም የሽንብራ ፍሬ አይደለም” ይሉኝ ነበር።የዚህ ጥበብ ኃይል አጅግ ብዙ ሚስጥራቶች ያዘለ  መሆኑ ጭምር።ለበሽታ ፈውስ የሚሆኑ ጥበቦችን የተለያዩ አፅዋቶችን በመቀመም ማግኘት አንደሚቻልና —የሚሰውር አፅ ሁሉ አንዳላቸው ነገሩኝ።ተገረምኩ።
 
         በርካቶች  አንደአንሽላሊት በቸለማ  አየመጡ ፈወስ ጠይቀው አግኝተዋል።—“ባጎረስኩ —” አንዲሉ ስነጋላቸው ግን ጠንቅዋይ ፣ደጋሚ አያሉ መቀመጫ አንዳሳጧቸውም ተረኩልኝ። ምን አንደሚያጣቅሱበት የማላውቀውን መፅሃፋቸው በተለያዩ ቀለማት ተዥጎርጉሮ ሕቡአ ፊደላት ፣ስአሎች ተስለውበት አይ ነበር። የ ብዙ ሚስጥራት ቁልፍ አንደሆነም ሳይነግሩኝ አላለፉም።የበለጠ በቀርብከዋቸው ቁጥር ብዙ ወደዱኝ።የ ጠልሰምን አውቀት ልያወርሱኝና ያለተረካቢ ሜዳ አንዳይቀር አንደሚያስተምሩኝ ቃል ገቡልኝ።አደረጉትም። አባቴ——-

                  “የዚህ ጠንቅዋይ በት መሄዱን ካልተውክ ቤት አንዳትገባ።”  ሲል ፎከር።የጥበብ ጣአም ገና በጠዋቱ ያጠጣሁት ልቤ የአባቴን ዛቻ ቦታ አልሰጠውም።  አየቆየ ግን —–

ፊታቸው መገርጣት ሲጀምር (በሽምግልና)፣አጆቻቸው ለብሩሽ አንክዋን ሲሰንፉ ሳይ ሳግ ይተናነቀኝ ነበር።

አንድ ቀን ላንጫ ኮረብታ ለመድኃኒት ቅመማ በሄዱበት ከዛፍ ላይ ወድቀው ሕይወታቸው ማለፉን ያወቅኩት ልፈልጋቸው ስሄድ ነበር።አንደዝያ ቀን አዝኘ አላውቅም።ከቀብራቸው በህዋላ ሰው ሁሉ አኔ አንዳስገደልክዋቸው ያስብ ነበር።የመንደሩን ወሬ አላስቀምጥ ሲለኝ ጥቂት መፅሃፎቻቸው ይዤ አዲስ አበባ ገባሁ።ለ 6 ዓመታት ከብዙ ሰው ጋር ስተዋወቅ የጠልሰም አውቀት ጨምሮ የሀገሬ ሕዝብ የዘነጋቸው በርካታ ጥበቦች አንዳሉ ተረዳሁ።
           ዛሬ ከ 6 ዓመታት በሁዋላ ————
ለዓመታት ጥበብ የታጨቀበት በት  ለማፍረስ ለተሰበሰበው ሰው አይኑ አንዲገለጥ ፈልግኩ ። ብዙ ለፍቼ አሳመንኩአቸው። በግልፅ ባይቃወሙትም  “ቤቱ አይፍረስ” የሚለውን ሃሳብ በውስጣቸው የጠሉ አይጠፉም።አኔም ከዘመናዊው የሕክምና ጥበብ አቆራኝቼ የርሳቸውን ፈለግ ለማስቀጠል ቃል ገባሁ። ቤቱም ታደሰ። ጥበብም ነገሠ ።ሁሌም አሸናፊ ነውና።

                                   (ናሙስ ናኒ ) 10/05/2006

2 thoughts on “”

  1. አንተ ልጅ አየህ ምናብህን ለምን እንደምወድልህ ታውቃለህ? ለነገሩ ተወው ብቻ ትችላለህ በተለይ ምናባዊ የታሪክ ስደራን ተክነheዋል
    በርታ!!!

    የጠልሰም እውቀትን መማር እፈልጋለሁ!!!

Leave a comment